ሲንየር አውቶ መካኒክ (Senior Auto Mechanics)

Application deadline closed.

Job Description

ኢትዮ ኢምፓክት ኮንሰልቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሲንየር አውቶ መካኒክ (Senior Auto Mechanics) ሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል:: 6 አመት እና ከዚያ በላይ ከሰሩ እንዲሁም ከዚህ በታች ያሉትን የሚያሟሉ ከሆነ ያመልክቱ::

የስራው መግለጫ፦

⦁ ቴክኒካዊ አገልግሎት መስጠት የተሽከርካሪዎችን ጥገና ማካሄድ፣
⦁ የተሽከርካሪዎችን ጥገና ወጪ ቆጣቢና የድርጅቱን አላማ በሚጠቅም ሁኔታ የውሳኔ ግብዓት ማቅረብ
⦁ የጋራዥን የጥገና ስራ ማከናወን ደህንነቱን መጠበቅ እንዲሁም የዕለት ተሽከርካሪዎች ክትትልእና የቴክኒካዊ የመካኒክ አገልግሎት በመስጠት የድርጅቱን የተሽከርካሪዎች አቅምን መጠቀም እንዲችል መርዳት እና የንዑስ ክፍሉን ስራ በብቃት መፈጸም እና የድርጅቱን የስራ አላማ ጋር በማቀናጀት የድርጅቱን ሕግና ደንብ ባገናዘበ ሁኔታና በተቀመጠው መረሃ ግብር እና ዓላማ መሰረት ስራውን መፈፀም

የስራ  ሃላፊነት፦

⦁ የንዑስ ክፍሉን ሠራተኞች /ኃላፊዎች በመርዳት የትራንስፖርትና የተሽከርካሪዎች ጥገና እንዲቀናጅ መስራት፣
⦁ አስፈላጊው የተሽከርካሪዎች ጥገና እና ሌሎች መረጃዎች አስመልክቶ ሰነዶቹና መረጃዎቹ እንድያዙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ መፈጸም፣
⦁ የተሽከርካሪዎች የጥገና ጥያቄ ሲቀርብ ፋይል ማድረግና ጥገናው እንዲፈፀም አስፈላጊውን ሁሉ እንዲደረግ መሰረት መከታተል፣
⦁ የተሽከርካሪዎች ስምሪት ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መርዳት ቴክኒካዊ እገዛ ማድረግ፣
⦁ በለቡ ማዕከል ወይም ሌላ ቅርንጫፍ የሚገኙትን የድርጅታችን ተሽከርካሪዎች እንደ ዋና መስሪያ ቤት ደህንነታቸው ሁኔታ መከታተል፣ማረጋገጥ፣ ሙያዊ ምክር መለገስ፣ እንዲተገበሩ ክትትል ማድረግ፣
⦁ ድርጅቱ ወይም ዋና ክፍሉ /ን/ክፍሉ የመንጃ ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ ቁጥር No 600/2008 እና ተዛማጅ ማሻሻያውን እንዲተገብርና ስራ ላይ እንዲያውል ሙያዊ ሀሳብ ማቅረብ ፍፃሜውን መከታተል፤
⦁ ያልተጠበቁ የመኪና ጥገና ጥያቄ ካሉ ተቀብሎ ለሚመለከተው አካል (ለቅርብ አለቃ) ማቅረብ መፍትሔ እንዲያገኝ መከታተል፤
⦁ የመከላከል ጥገናን ለመከናወን የውሳኔ ግባት መቅረብ ሲወስን መተግበር፤
⦁ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች አመታዊ ምርመራ እንዲደረግላቸው የበኩሎን አስተዋጾ ማድረግ፣
⦁ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች እለታዊ፣ ብልሽት ሲገጥማቸው በውጪ ወይም በውስጥ መጠገን መቻላቸውን አግባብ በሆነ ፎርም ወይም ቅጽ ሞልቶ ማሳወቅና እንዲጸድቅ ማድረግ፣
⦁ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች መጠገን፣ ማደስ እና አዲስ የተገዙ መለዋወጫዎችን አረጋግጦ በትክክል መግጠም አሮጌዎቹ ደግሞ ወደ ትክክለኛ ቦታ ሄዶ እንዲቀመጡ/እንዲገቡ ማድረግ፣
⦁ የመካኒክ ሙያዊ አገልግሎት መስጠት መለስተኛ የሞተር ጥገና ማካሄድ፣ ግር ቦክስ መጠገን፣ ፍርሲዮን መቀየር፣ የእጅ ወይም የእግር ፍሬን ማስተካከል፣ የተሽከርካሪዎችን የውጭአካል ጥገና ማከናወን ወዘተ…
⦁ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች ሰርቪስ የቅድመና የድህረ ቴክኒካዊ ምርመራ ማካሄድ እና ወጪን ያማከለ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፣
⦁ የዕለት በዕለት የውስጥ ጋራዥ የተሽከርካሪዎች ጥገና ማካሄድ፣
⦁ የውስጥ ጋራዥ የስራ ቦታን ንጽህናን ደህንነት (Saftey) በደንብ መጠበቅ ደንቦችና ህጎችን መተግበር፣
⦁ ከተሽከርካሪዎች ጥገና በኋላ የተመለሰውን የዕቃዋች ዝርዝር መዝግቦ መያዝ የነበሩትን ለይቶ መያዝ ምንም አይነት ጥቅም የማይሰጡትን ለይቶ እንዲጣሉ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፣
⦁ አስፈላጊ የውስጥ ጋራዥ ፋሲሊቲዎችን/ዕቃዎችን መለየትና መጠየቅ ከተሟሉ በኋላ በትክክል መያዝ እና ስራ ላይ ማዋል፣
⦁ ሙያዊ እና በትክክል የተሽከርካሪ የጥገና ወጪ መለየትም ለጥገና የዋሉትን የነዳጅ ወጪ ፣ የጥገና ወጪ፣ የዘይትና ሊሎች ሉብርካንቶች ወጪ በሎግ መዝገብ (Log Books) ላይ እንዲመዘገቡና እንዲያዙ ማድረግ፣
⦁ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወቅቱን ጠብቆ የሚደረገውን የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች ነዳጅ አጠቃቀም በዕድሚያቸው እና በአገልግሎት ዘመናቸው ላይ በመመርከዝ ጥናት እና ዳሰሳ በሚደረግበት ጊዜ መሳተፍ እና ሙያዊ ዕገዛ ማድረግ፣
⦁ የድርጅቱ የተሽከርካሪ አይነት እና ልዩ ባህሪ በመዳሰስ የመለዋወጫ ዕጥረት እንዳይፈጠር የውሳኔ ሀሳብ በመስጠት ሂደቶች ላይ መሳተፍ ተገቢውን መፍትሄ መጠቆም፣
⦁ የድርጅቱን ተሽከርካሪዎች/ ኃላፊዎችንም ሆኑ ሠራተኞች የአሽከርካሪነት መሠረታዊ የመካኒክ/ ቴክኒካዊ ሁኔታዎች አዲስ መርዎች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣
⦁ የውጭ ጋራዥ አገልግሎት ከመኪኖቹ ባህሪ ጋር በማገናዘብ ብቁ የሆኑትን ከንዑስ ክፍሉ ጋር ደሰሳ ጥናት በማድረግ የውሳኔ ሀሳብ መቅረብ፣
⦁ ከባድ የተሽከርካሪዎች የጥገና ወይም የጉዳት ጥገና ጥያቄና ሁኔታ ለቅርብ አለቃ ወይም ለሚመለከተው የድርጅቱ አካል በሰዓቱ ሪፖርት ማድረግ ቴክኒካዊ ምክር መሰጠት፣
⦁ ከአቅም በላይ ለሆኑ ጥገናዎች ወይም ጥያቄዎች የንዑስ ክፍል ኃላፊውን እርዳታ ወይም እገዛ መጠየቅ የጋራ የቴክኒክ ወይም ሙያዊ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣
⦁ አጠቃላይ የጋራዥ የጥገና ስራ እና አገልግሎቶች ቢያንስ በሳምንት አንዴ ሪፖርት ማድረግ፣ መሳወቅ፣
አስፈላጊውን የተሽከርካሪዎች መረጃ ወይም ቴክኒካዊ ሁኔታዎች በሚጠየቁበት ጊዜ መዘጋጀት ሪፖርት ማድረግ፡፡

መስፈርቶች፦

  • በአወቶ መካኒክስ ዲፕሎማ እና 10ኛ ወይም 12ኛ ያጠናቀቀ
  • የአውቶ መካኒክ ስልጠና ሰርቶፍኬት ያለው
  • 3ኛ ደረጃ ወይም ከዛ በላይ ተገቢ መንጃ ፍቃድ ያለው
  • መሠረታዊ የኮምፒውተር ዕወቀትና ልምድ ያለው
  • 6 ዓመት በታወቀ ድርጅት ወይም ጋራዥ በመካኒክ የሰራ እንዲሁም የስራ ልምድ ያለው/ያላት
  • ሥራዎችን በተፈለገው ቀንና ሰዓት የመፈጸም አቅምና ችሎታ
  • ከፍተኛ የቴክኒካዊ ብቃት/የመካኒክ
  • የተለያዩ ችግሮችን የመገንዘብ እና መፍትሄ የመስጠት አቅም፣
  • ሥራን ከመደበኛ ሰዓት ውጪ ለመፈጸም/ለመጨረስ ተነሳሽነት እና ዝንባሌ
  • የመመርመር ፍላጎትና ክህሎት፣
  • መሠረታዊ የመጻፍ የማንበብ እና የመግባባት ክግሎት እና ችሎታ፣
  • ተነሳሽነት በራስ መመራት፣ ጥሩ ከቡድኖች ጋር የመስራት ባህሪ እና አቅም፣
  • የደንበኛ አገልግሎት እና አፋጣኝ መልስ/መፍትሄ የመስጠት አቅም
  • ለድርጅቱ እሴቶች አላማዎች እና ንብረት ታማኝነትና ተቆርቋሪ