Job Description
ኢትዮ ኢምፓክት ኮንሰልቲንግ ለየግል መስሪያ ቤት በየፈርኒቸር ገጣጣሚ የስራ መደብ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በቴክኒክና ሙያ /TVET/ የትምህርት ዘርፍ በእንጨት ስራ በደረጃ 3 ወይንም/10+3/10+4/ ሰርተፊኬት ያለው /ያላት 2 ዓመትና ከዚያ በላይ በሙያው የሰራ/ች እዚህ ላይ ያመልክቱ፡፡
DUTIES AND RESPONSIBILITIES
● በፍጥነት እና በጥራት ስራን ማከናወን፣
● ለሚቀጥለው ቀን የተሸጡ እቃዎችን በንዑስ ክፍል ኃላፊና ትዕዛዝ መሠረት እቃዎችን ማዘጋጀት፣
● የተሸጡ እቃዎችን በደረሰኝ መሠረት የእቃ ማስረከቢያ ሰነድ (Delivery Note /Do) መሰረት ማፅደቅ፣ የደንበኛውን አድራሻ መቀበልና እቃው ከመጫኑ እንዲሁም ከግቢ ከመውጣቱ በፊት ደንበኞች ጋር ደውሎ ማሳወቅ፣
● በእቃ ማስረከቢያ ሰነድ (Delivery Note /Do) መሠረት የሚጫኑት እቃዎች ትክክል፣ ንፁህና የተሟሉ መሆናቸውን አረጋግጦ መጫንና አብረው ያሉትን የፈርኒቸር መገጣጠሚያ ረዳቶች በማስተባበር ማዘጋጀት፣
● እቃው የሚሄድበት ቦታ (ደንበኛው) ቢሮ/ቤት እንደተደረሰ ከደንበኛው ጋር ግንኙነት በማድረግ ከፈርኒቸር መገጣጠሚያ ቡድን መሪዎችና ረዳቶች ጋር በመተባበር ማውረድና ለገጠማ ዝግጁ ማድረግ፣
● ደንበኞች ጋር ያደረሱትን እቃ በደንበኛው ፍላጐት መሠረት በትክክል ገጥሞ፣ የእቃ ማስፈረሚያ ሰነድ (Delivery Note) አስፈርሞ ማስረከብ፣
● የገጠማ ስራው እንደተጠናቀቀ የደንበኛ አስተያየት መስጫ እንደተሞላ ማረጋገጥ ፣
● ዕቃ ያስረከበበትን ሰነድ (Delivery Note) እንዲሁም የደንበኞች አስተያየት መስጫ ፎርም (Customer’s Comment Form) ቁጥሩን መዝግቦ ለስርጭትና ከሽያጭ በኋላ አገልግሎት ለአስተባባሪ በወቅቱ ማስረከብ፣
● በማንኛውም የገጠማና የደሊቨሪ ስራ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለንዑስ ክፍል አስተባባሪው ወዲያውኑ በፁሁፍ ማሳወቅ፣
● ያላለቁ የስራ ሁኔታዎችን (ያልተገጠሙ) እቃዎች ካሉ ፕሮግራም አስይዞ ወዲያው እንዲጠናቀቅ ማድረግ፡
● ስራውን አጠናቀው እንደመጡ በክፍሉ የተዘጋጀው ቅጽ ላይ ሪፖርት መፃፍ፣
● በቅርብ የስራ ኃላፊውና ከበላይ ኃላፊዎች የሚሰጣቸውን ስራዎች በጥራትና በቅልጥፍና ማከናወን፣
REQUIREMENTS
– በቴክኒክና ሙያ /TVET/ የትምህርት ዘርፍ በእንጨት ስራ በደረጃ 3 ወይንም/10+3/10+4/ ሰርተፊኬት ያለው /ያላት
– 2 ዓመትና ከዚያ በላይ በሙያው የሰራ/ች
– በእንጨት ስራ ዘርፍ የሰራ ቢሆን ይመረጣል